የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2011 ዓ.ም የ1ኛው ዙር ውድድር መርሃ ግብርን መሠረት የአደረገ ምርጥ አስር ተጨዋቾች ምርጫ ኘሮጀክት ከገምጃ የህትመትና ማስታወቂያ ሥራዎች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር ለመሥራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን መግለጻችን ይታወሳል፡፡

በምርጥ 10 ዕጩነት በምርጫው የሚካተቱ 32 ተጨዋቾችን የመምረጡን ሥራ ከፌዴሬሽኑ የቴክኒክና ልማት ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ተሠርቶ ተጠናቋል፡፡  

32ቱ እጩ ተጫዋቾቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

ተራ ቁጥር የተጫዋች ስም ክለብ የሚጫወትበት ቦታ
1 አማኑኤል ገ/ሚካኤል መቐለ 70 እንድርታ አጥቂ
2 ሐይደር ሸረፋ መቐለ 70 እንድርታ አማካይ
3 አዲስ ግደይ ሲዳማ ቡና አጥቂ
4 ፊቶዲን ጀማል ሲዳማ ቡና ተከላካይ
5 አቤል ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ
6 ሳላዲን ሰይድ ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ
7 ታፈሰ ሰሎሞን ሐዋሳ ከተማ አማካይ
8 ደስታ ዮሃንስ ሐዋሳ ከተማ የመስመር ተከላካይ
9 ያሬድ ባዬ ፋሲል ከነማ ተከላካይ
10 ሱራፌል ዳኛቸው ፋሲል ከነማ አማካይ
11 ኤልያስ አህመድ ባህር ዳር ከተማ አማካይ
12 ወሰኑ ዓሊ ባህር ዳር ከተማ አጥቂ
13 ዳዋ ሆቴሳ አዳማ ከተማ አጥቂ
14 ከነዓን ማርክነህ አዳማ ከተማ አጥቂ
15 አቡበከር ነስሩ ኢትዮጵያ ቡና አጥቂ
16 አማኑኤል ዮሃንስ ኢትዮጵያ ቡና አማካይ
17 ደስታ ደሙ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተከላካይ
18 አፍወርቅ ሀይሉ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተከላካይ/ተመላላሽ
19 ምኒሉ ወንድሙ መከላከያ አጥቂ
20 ዳዊት እስጢፋኖስ መከላከያ አማካይ
21 ባዬ ገዛኸኝ ወላይታ ዲቻ አጥቂ
22 ቸርነት ጉግሳ ወላይታ ዲቻ አማካይ
23 ሳሙኤል ዮሃንስ ድሬዳዋ ከተማ ተከላካይ/ተመላላሽ
24 ያሬድ ሙሸንዲ ድሬዳዋ ከተማ አማካይ
25 አስቻለው ግርማ ጅማ አባ ጅፋር አጥቂ
26 ይሁን እንዳሻው ጅማ አባጅፋር አማካይ
27 ሄኖክ አየለ ደቡብ ፖሊስ አጥቂ
28 ዮናስ በርታ ደቡብ ፖሊስ አማካይ
29 ጅላሉ ሻፊ ስሑል ሽረ አማካይ
30 ልደቱ ለማ ስሑል ሽረ አጥቂ
31 የአብስራ ተስፋዬ ደደቢት አማካይ
32 አቤል ጥላሁን ደደቢት አማካይ

በቀጣይ የተጫዋቾች መምረጫ የጽሁፍ ቁጥሩን እና የተጫዋቾቹን ኮድ በይፋ በቀጣይ ቀናት እንደሚያሳውቁ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ታፈሰ ገልጸውልናል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here