የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የከፍተኛ እግር ኳስ አሠልጣኞች ሥልጠና ራባት በሚገኘው የሞሮኮ ፌዴሬሽን ዘመናዊ የእግር ኳስ አካዳሚ ይካሄዳል፡፡

ከነሐሴ 29/2009 ዓ.ም እስከ መስከረም 7/2010 ዓ.ም ለ14 ቀናት የሚካሄደው ስልጠና ለኢትዮጵያውያን ብቻ የተዘጋጀ ሲሆን ከኢትዮጵያ ወንዶች እና ሴቶች ኘሪሚየር ሊግ እንዲሁም ከከፍተኛ ሊግ ክለቦች የተወከሉ 20 አሠልጣኞች እንደሚሳተፉበት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለሥልጠናው ሠልጣኞች እና ክለቦቻቸው የትራንስፖርት ጪያቸውን ብቻ  የሸፈኑ ቢሆንም ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎችን የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በመሸፈን እንዲያዘጋጅ የተደረገው ስምምነት በአቻ ፌዴሬሽኖች መካከል መልካም የሥራ ግንኙነቶችን በመፍጠርና የልምድ ልውውጥን ለማዳበር ጠቀሜታውን የጐላ እንደሚያደርገው ይታመናል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here