በኢትዮጵያ ወንዶች ኘሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት በወጣው ኘሮግራም መሠረት በሐዋሳ ከተማ ሊካሄዱ የነበሩ ሁለት ጨዋታዎች በፀጥታ ችግር ምክንያት ሳይካሄዱ መቅረታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከቀሩት ሁለት ጨዋታዎች መካከል አንዱ ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው የደቡብ ፖሊስ እና የወላይታ ድቻ ጨዋታ በዕለቱ በተፈጠረው የደጋፊዎች ፀጥታ ችግር ምክንያት ለሚያዚያ 17 ቀን/2011 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት  በአዲስ አበባ ስታዲየም በዝግ ስታዲየም እንዲካሄድ የተወሰነ መሆኑን እና  ሁለተኛነት ሚያዚያ 13 ቀን 2011 ዓ.ም  ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ሊካሄድ የነበረው ሐዋሳ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በፀጥታ ጉዳይ የክለቡ አመራር ከፀጥታ ኃይሉ አቅም በላይ እንደሆነና ውድድሩን በዕለቱ ማካሄድ እንደማይቻል ከጨዋታው ኮሚሽነር የቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ የኘሮግራም ለውጥ አድርጐ በገለልተኛ ሜዳ ሚያዚያ 17 ቀን 2011 ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በአሰላ ስታዲየም እንዲስተናገድ የሊግ ኮሚቴ ውሳኔውን አስተላልፋል፡፡

የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የሊግ ኮሚቴው በተደረገው ውሳኔ ቅሬታ እንዳለው በመግለጽ ጨዋታው በዝግ ስታዲየም እንዲደረግለት ጥያቄ ቢጠይቅም የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎች ምንም ጥፋት ያላጠፋ ስለሆነ ደጋፊዎችን በመቅጣት በዝግ ውድድር ለማድረግ ምንም የህግ አግባብ አለመኖሩን በመጥቀስ ጨዋታው በወጣው ኘሮግራመ መስተናገድ እንደሚገባው የሊግ ኮሚቴ ውሳኔውን የሰጠ መሆኑን ገልጾልናል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here