የፌዴራል ፖሊስ እግር ኳስ ክለብ ከ አቃቂ ቃሊቲ እግር ኳስ ክለብ ጋር የነበረው ጨዋታ ላይ የዳኝነት ሂደትን አስመልክቶ በ16/8/2011 ዓ.ም በተፃፈ በደብዳቤ ቅሬታውን ክለቡ አሳውቋል፡፡ ለክለቡም  የሚከተለው ምላሽ ተሰጦታል፡፡

  1. ክለባችሁ በ29/7/2011 ዓ.ም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ ጋር ስትጫወቱ የእለቱ የውድድር ኮሚሽነር ስለጨዋታው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ውድድሩ በሰላም ተጀምሮ መጠናቀቁንና በዳኝነት አፈፃፀም ላይ ምንም አይነት የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን በማረጋገጣቸው፤
  2. በ13/8/2011 ዓ.ም ከአቃቂ ቃሊቲ እግር ኳስ ክለብ ጋር በነበራችሁ ጨዋታ ላይ ለአንድ ቡድን ያዳላ ፍፁም የህሊና ዳኝነት ያልነበረበት በማለት የእለቱን ዳኛ ከመኮነን አልፎ ተገቢ ያልሆነ ቅጣት ተሰጥቶብን ጐል ተቆጥሮብን እንድንሸነፍ ተደርጓል በማለት ቅሬታ ያቀረባችሁ ቢሆንም የእለቱ የጨዋታ ኮሚሽነር ባቀቡት ሪፖርት ላይ ለአቃቂ ቃሊቲ ቡድን የተሰጠው ቅጣት ምትና የፀደቀው ግብ የጨዋታ ሕግ ሳይጣስ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በመሆኑም የሚቀርብ የዳኝነት ቅሬታ ካለም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲኘሊን መመሪያና በከፍተኛ ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ሕጉን ተከትሎ በጨዋታው ወቅት የክስ ሪዘርቭ ተመዝግቦ ወደ ፅሁፍ ተቀይሮ መቅረብ የሚገባው ሲሆን ጥያቄው ይህን መሠረት አድርጉ ያልቀረበ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያሳውቃል፡፡

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here