የኢትዮጵያ ሴቶች እና ወንዶች ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኖች ለቶኪዮ 2020 ውድድር የማጣሪያ ጨዋታቸውን በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኖችን አስመልክቶ ነገ ሚያዚያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቷል፡፡ በዚሁ መሠረት የመገናኛ ብዙሃን በሙሉ በኘሮግራሙ ላይ ተገኝተው ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

ማስታወሻ

  • 10፡00 – 10፡30 ሰዓት የወንዶች ኦሎምፒክ ቡድንን በተመለከተ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ እና አምበል  እንዲሁም
  • 10፡30 – 11፡00 ሰዓት የሴቶች ኦሎምፒክ ቡድንን በተመለከተ የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሠልጣኝ እና አምበል በቦታው በመገኘት መግለጫውን ይሰጣሉ፡፡
አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here