የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለኢትዮጵያ ሴቶች ኦሎምፒክ ቡድን አሠልጣኝ ቅጥር ሊያካሂድ ሲሆን  ምዝገባው የካቲት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ የጠናቀቅ ይሆናል ፡፡ በማስፈርቱ ሴቶችን ብቻ የሚጋብዝ ቢሆን ተጨማሪ መስፈርቶቹ

  • በኘሪሚየር እና 2ኛ ሊግ ላይ 3 ዓመት ከዚያ በላይ ያገለገለች፣
  • ባለፋት ሦስት ዓመታት ውስጥ በማሰልጠን ውጤታማ የሆነች፣
  • የት/ደረጃ 10ኛ ወይም 12ኛ ወይም ከዚያ በላይ የሆነች
  • የማሠልጠን ላይሰንስ B እና ከዚያ በላይ
  • ከካፍ ቋንቋዎች አንዱን ማንበብ፣ መፃፍ እና መናገር የምትችል፣
  • አስተዳዳራዊና የሥልጠና ዕቅድ የምታቀርብና የምታስረዳ፣
  • የቡድን አደረጃጀትና አሠራርን በብቃት መወጣት የምትችል፣
  • በዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነች፣
  • በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዕውቅና ባላቸው የአሠልጣኝነት ሥልጠና ኮርሶች ላይ የተካፈለች አሠልጣኝን የሚመርጥ ሲሆን ደሞወዝን በተመለተ በስምምነት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here