የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሚያካሂደው የኘሬዚዳንትነት እና የሥራ አስፈፃሚዎች ምርጫ የምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራውን መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሲከናወኑ የቆዩትን ዝርዝር ስራዎች እና የተመዘገቡትን ውጤቶች ይፋ ለማድረግ የምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ ዓርብ ህዳር 6 ቀን 2010 ዓ.ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል /አዲሱ ህንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ/ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫውን ሁሉም የስፓርት መገናኛ ብዙሃን እንዲዘግቡት በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡

አጋራ
Profile photo of የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here