ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያዘጋጀው ውይይት በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ፤ በሸራተን አዲስ ሲካሄድ የቆየው ውይይት 9ኝ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያ የሚመለካታቸው ባለድርሻ አካላት የማጠቃለያ ሀሳብ ሠጠዋል፡፡

ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ የባህል እና ቱሪዝም ሚኒሰቴር ሚንስትር ዴታ ” መንግስት መግባት ያለበት ቦታ አለ ነገር ግን በትልቁም በትንሹም ገብተን አንፈተፍትም። ስለ ስፖርታችን ታሪካዊ አመጣጥ ሰነዶችን አገላብጠን ያየን አይመስለኝም፤ የትምህርት እና ስልጠናው ፍኖተ ካርታ ላይ እንዲካተት ስፖርቱን እያደረግን እንገኛለን፤ ስፖርት አደረጃጀት ታክቲክ እንጂ ስትራቴጂ አይደለም፤ 56 ሀገራት ተሞክሮን አይተናል 26 ሀገሮች ባህል እና ቱሪዝም ጋር እንዲሁም 6 ሀገራት ናቸው በሚኒስቴር ደረጃ ያዋቀሩት፤ ስፖርቱ በሚኒስቴር ደረጃ ስለተመራ አይደለም ለውጥ የሚመጣው፤ ኢትዮጵያ ልትፈርስ አትችልም”

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው” ይህንን ውይይት መድረክ ላዘጋጁት የቅዱስ ጊዮርጊስ አመራሮች ምስጋና አቀርባለሁ። ውይይቱ አንድ ስድስት አካላት ላይ ያርፋል። ጉዳዮችን በደንብ አውጥቶ መወያየት ያስፈልጋል። ስፖርት ለሰላም ለፍቅር የሚለው ሳይሆን ለትግል የሚለው ነው ገኖ የወጣው ምንም አይነት አይነት ቴክኖሎጂ ቢያጅበን ስፖርት ለፍቅር ለአንድነት ለመቻቻል ካልሆነ አደጋ አለው። ስፖርት ሁሉም ነገር ነው፤ ስፖርት ሳይንስ ነው፤ ስፖርት አርት ነው፤ ስፖርት ባህል ነው ስፖርት እውቀት ነው ስፖርት ክህሎት ነው፤ ስፖርት ሁሉ ነገር ነው። ሁሉን ነገር ትተን ስራችንን በፍቅር ብናስኬድ የተሻለ ነው። የስፖርት ጨዋነት ምንጮችን ከዛሬ30 እና 50 ዓመት ያለንን ነገር ብንመለከት መፍትሄ ይሆናል።

የኢእፌ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ” ቅዱስ ጊዮርጊስ ይህንን ሀላፊነት ወስዶ ሲደውልልኝ እኔ ነኝ ወደሱ ቢሮ የመጣሁት፤ ሜኑ ቀርቦለት በፈለገበት ባህል እና ቋንቋ የተወለደ የለም ካላችሁ ንገሩኝ፤ ነገሮችን ከመግፋት ወደ እኛ መውሰድ አለብን፤ የተሳሳተን ዳኛ እንደ ነፍሰ ገዳይ ምናየው ለምን እንደሆነ አይገባኝም እንዲህ ከሆነ በእጁ እንግሊዝ ላይ ያገባውን ማራዶናን አርጀንቲና ሄደን ልንገለው ነው ማለት ነው፤ ስህተቱ ሆንተብሎ የተሰራ ከሆነ ነው ችግሩ። ዳኛ ስንመድብ ዘር እየቆጠሩ ተቸግረናል፤ ሚስቱ እንትን ናት አባቱ ከዚያነው መባል ተከምሯል ይህ በጣም ያሳፍራል፡፡ አንድን ክለብ ለመበደል አንዱን ለመጥቀም አይደለም፤ ክለቦች ጋር የተነሳው ችግር ሜዳዎቻችን ችግር ያሉባቸው ናቸው፤ ይህንን ለማረም እንሞክራለን። የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ፌደራል ፖሊስ ጊቢ ውስጥ ነው የተፈጠረው፤ ሽምግልና ምትመጡ አመራሮች አላችሁ። ፕሮግራም ስናወጣ ግልጸኝነት በተሞላበት መልኩ ነው እየሰራን ያለነው። ሊግ ካምፓኒ መስርቱ ሲባል ሚያፈገፍግ ክለብ ብቻ ነው ያለው። የእግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የሌሎችን ማንዴት ለዩ። በተለምዶ ውስጥ ስላለን ነው እንጂ ብዙ መሻሻል ያለባቸው ነገሮች አሉ። አንዳችን አንዳችን ውስጥ ሆነን ምንገመግመው። በጥናቱ መሰረት የሰው ሀይል እያሟላን ነው። ዶ/ር እያሱን ጽፈት ቤት ሀላፊ አርገን ስናመጣ 4 ወር አጥንቼዋለሁ መልኩን ጭራሽ አላቀውም ነበር። ስለእውነት እስካሁኗ ሰዓት ዘሩ ምን እንደሆነ አላውቅም። በአንድ ጊዜ ይህንን ህዝብ ማርካት አይቻልም። አብዛኞቹን ግብዓት አድርጌ እወስዳለሁ። ሚዲያ መስታውታችን ነው ነገር ግን ስብዕናን የሚነኩ ከሆነ ልክ አይደለም። ተያይዘን ከተነሳን ተያይዘን እናድጋለን። ክለቦች ሀብት እንዲኖራችሁ አድርጉ። እኔን የሚገነቡኝ ነገር አግኝቻለሁ አመሰግናለሁ።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ አብነት ገብረ መስቀል ” ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ስፖርት መርህ እየተጓዘ ይገኛል፤ ጥሩ የሁለት ቀን ውይይት ተደርጓል። ይህ አይነት ውይይት ወደፊትም ይቀጥል። ለህግ እና ለመርህ ተገዢ ለመሆን እንስራ”

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን” መድረኩ አላማውን አሳክቷል፤ ሁላችንም የሚያስተሳስረን ኢትዮጵያዊነት አለ፤ ዛሬ ደስታ ተሰምቶኛል “

ፕሮግራሙ ለዝግጅቱ መሳካት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን በማመስገን ተጠናቋል።

አጋራ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ነው። በ1943 እ.ኤ.አ. የተመሠረተ ሲሆን፣ በ1953 እ.ኤ.አ. የፊፋ፣ እንዲሁም በ1957 እ.ኤ.አ. የካፍ (CAF) አባል ሆነ። ይህ አካል የብሔራዊ እግር ኳስ ሊግን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንን ያቀናጃል።

ምላሽ ይተው

Please enter your comment!
Please enter your name here